አል ነስር ድል አድርጓል ! በሳውዲ አረቢያ ሊግ አል ነስር አል ዲሪያህን 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል። የአል ነስርን የማሸነፊያ ግብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ፣ ሳሙ እና ኪንግስሌይ ኮማን ማስቆጠር ችለዋል። ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግርኳስ ህይወቱ 980 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል። አል ነስር በሊጉ የሰበሰባቸውን ነጥቦች አስራ ዘጠኝ በማድረስ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። በቀጣይ መርሐ ግብር አል ነስር ከአል አህሊ ጋር ይጫወታል። @tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ስፖርት ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የስፖርታዊ መረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። በዚህ ቻናል ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ የስፖርት መረጃዎች ይዳሰሱበታል። ለመረጃ እና ማስታወቂያ +251926797469
Динамика подписчиков
с 20 июля 2026 по 12 октября 2026 · минимум 288 000 · максимум 291 000
Кто рекламировался за полгода
Рекламных размещений с маркировкой не найдено.
Публикации
አል ነስር ለሮናልዶ ድጋፍ ያሳያል ! የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ነስር በዛሬው ጨዋታ ለክርስቲያኖ ሮናልዶ ድጋፍ ለማሳየት ማቀዱ ተነግሯል። አል ነስር ለክርስቲያኖ ሮናልዶ በስታዲየሙ ውስጥ የድጋፍ ባነር ለማሳየት ማቀዱ ተገልጿል። በተጨማሪም በስታዲየሙ ለደጋፊው ለሮናልዶ ድጋፍ የሚያሳዩ ወረቀቶች እንደሚሰራጩ ተዘግቧል። አል ነስር ዛሬ ምሽት 3:00 ሰዓት ከአል ዲሪያህ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል። …
“ ህመሙ አሁንም ጨጓራችን ውስጥ አለ ” አርቴታ የመድፈኞቹ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የብራይተን ሽንፈት እስካሁን ከውስጣቸው እንዳልወጣ ተናግረዋል። “ ህመሙ አሁንም በጨጓራችን ውስጥ አለ ” ያሉት አርቴታ “ ነገ በዚህ ህመም እንጫወታለን ምክንያቱም መማሪያ ሆኖናል " ብለዋል። አክለውም " ከዛ ጨዋታ ብዙ ነገሮችን ተምረናል ጥሩ ከሆነው ቡድን ጋር መሰረታዊ ነገሮች አላሳካንም " ሲሉ ገልጸዋል። አርሰናል ነገ 8:30 ከሊድስ ዩናይትድ ጋር የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። @tikvahethsport @kidusyoftahe
ቱርክ ከአሰልጣኟ ጋር ተለያየች ! የቱርክ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቪንሴንዞ ሞንቴላን ከሀላፊነታቸው ማሰናበቱ ተገልጿል። አሰልጣኙ ቡድኑን እየመሩ በአለም ዋንጫ እና ኔሽንስ ሊግ ጨዋታዎች ጥሩ ያልሆነ ጊዜ ማሳለፋቸው አይዘነጋም። ቱርክ በአሰልጣኙ እየተመራች በኔሽንስ ሊግ ያደረገቻቸውን አራት ጨዋታዎች በሽንፈት አጠናቃለች። ብሔራዊ ቡድኑ በአራት ጨዋታዎች 11 ግብ ሲቆጠረበት ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል። @tikvahethsport @kidusyoftahe
አል ነስር ለሮናልዶ ድጋፍ ያሳያል ! የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ነስር በዛሬው ጨዋታ ለክርስቲያኖ ሮናልዶ ድጋፍ ለማሳየት ማቀዱ ተነግሯል። አል ነስር ለክርስቲያኖ ሮናልዶ በስታዲየሙ ውስጥ የድጋፍ ባነር ለማሳየት ማቀዱ ተገልጿል። በተጨማሪም በስታዲየሙ ለደጋፊው ለሮናልዶ ድጋፍ የሚያሳዩ ወረቀቶች እንደሚሰራጩ ተዘግቧል። አል ነስር ዛሬ ምሽት 3:00 ሰዓት ከአል ዲሪያህ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል። @tikvahethsport @kidusyoftahe
#EthPL 🇪🇹 በ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ሀላባ ከተማ ከወልዋሎ ዓ.ዩ ጋር 1ለ1 ተለያይተዋል። ለአዲስ አዳጊው ሀላባ ከተማ ሽመክት ጉግሳ ሲያስቆጥር ካርሎስ ዳምጠው ወልዋሎ ዓ.ዩን አቻ አድርጓል። ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ? አርብ - ባሕርዳር ከተማ ከ ሀላባ ከተማ ( ሀላባ ) - ወልዋሎ ዓ.ዩ ቀጣይ ሳምንት በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ጨዋታ ምክንያት የሊግ ጨዋታ አያደርግም። @tikvahethsport @kidusyoftahe
ካፍ ውሳኔውን ሊቀይር መሆኑ ተነገረ ! የአፍሪካ እግርኳስ የበላይ አስተዳዳሪ ካፍ የአፍሪካ ዋንጫን በየ አራት አመቱ ለማድረግ መወሰኑ ይታወቃል። ይሁን እንጂ ካፍ በአሁኑ ሰዓት ውሳኔውን ለመለወጥ ውይይት ላይ እንደሚገኝ የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ ተናግረዋል። ካፍ የአፍሪካ ዋንጫ ውድድርን እንደ ቀደመው ጊዜ መልሶ በየሁለት አመቱ ለማድረግ ማሰቡ ተነግሯል። ካፍ የአፍሪካ ዋንጫውን በ 2027 እና 2028 ካደረገ በኋላ በየአራት አመቱ ለማድረግ ወስኖ ነበር። የካፍ ስራ አስፈፃሚ በቀጣዩ ስራ አስፈፃሚዎች ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ውሳኔውን እንደሚፈትሽ ተገልጿል። @tikvahethsport @YisakAH
“ ድሉ ያስፈልገናል “ ዣቢ አሎንሶ የሰማያዊዎቹ አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ቡድኑ ከበርንማውዝ ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ ማሸነፍ እንደሚፈልግ ገልጸዋል። “ በርንማውዝ የራሱ ማንነት ያለው ቡድን ነው ” ያሉት አሎንሶ “ ከባድ ቡድን ነው ነገርግን ማሸነፍ እንፈልጋለን ድሉ ያስፈልገናል "ብለዋል። ስለ ማንችስተር ሲቲ ክስ የተጠየቁት ዣቢ አሎንሶ “ መረጋጋት እና የመጨረሻውን ውሳኔ ማየት አለብን “ ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። ስለ ተጨዋቾች ጉዳት የተናገሩት ዣቢ አሎንሶ ሪስ ጄምስ ፣ ፓልመር ፣ ጇ ፔድሮ እና ፓሌስትራ ወደ ሜዳ ተመልሰዋል ብለዋል። ሞይሰስ ካይሴዶ በተመሳሳይ ለጨዋታው ዝግጁ መሆኑን ያስረዱት አሰልጣኙ ጥንቃቄ እናደርግለታለን ሲሉ ገልጸዋል።…
አዳማ ከተማ አመቱን በድል ጀምሯል ! በ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1ለ0 አሸንፏል። የአዳማ ከተማን የድል ግብ አጥቂው ቢኒያም አይተን በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል። ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ? አርብ - ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ከ ነገሌ አርሲ ( አዲስ አበባ ከተማ ) አርብ - አዳማ ከተማ ከ ሸገር ከተማ ( አዳማ ከተማ ) @tikvahethsport @kidusyoftahe
ዩናይትድ የተጫዋቾቹን ግልጋሎት አያገኝም ! ማንችስተር ዩናይትድ ነገ ከቶተንሀም በሚያደርገው ጨዋታ የተጫዋቾቹን ግልጋሎት አያገኝም። በጨዋታው ቤንጃሚን ሼሽኮ ፤ ፓትሪክ ዶርጉ እና ማዝራዊ እንደማይሳተፉ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ተናግረዋል። “ ዶርጉ ለበርካታ ሳምንታት ከሜዳ ይርቃል " ሲሉ ማይክል ካሪክ አሳውቀዋል። በሌላ በኩል አማድ ዲያሎ ፣ ማርከስ ራሽፎርድ እና ኮቢ ማይኖ በቡድኑ ስብስብ…